ለገና የእንስሳት ተዋፅዖ እና የፍጆታ እቃዎችን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በቅናሽ አቀርባለሁ...

ለገና የእንስሳት ተዋፅዖ እና የፍጆታ እቃዎችን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በቅናሽ አቀርባለሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  የፊታችን ሀሙስ ለሚከበረው የገና በዓል የግብርና ምርቶችን ጨምሮ የተለያዩ የእንስሳት ተዋጽዖ እና ሌሎች የፍጆታ እቃዎችን ለሸማቹ ማህበረሰብ በሕብረት ሥራ ማኅበራት ሱቆች ለማቅረብ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሕብረት ሥራ ኤጀንሲ እና በአማ ራ ክልሎች ከሚገኙ አምራች ዩኒየኖች ጋር የገበያ ትስስር በመፍጠር ከ19 ሺኅ ኩንታል በላይ ጤፍ ፣ 4 ሺኅ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት፣ ከ180 የበላይ የእርድ በሬዎች፣ ከ1 ሚሊዮን በላይ እንቁላል፣ እንዲሁም ከ1 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት እና ከ3 ሺኅ 500 ኪሎ ግራም በላይ የቅቤና አይብ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ለማቅረብ የቅድመ ዝግጅት ስራውን መጠናቀቁን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብነህ እምሩ ይፋ አድርገዋል።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የሕብረት ሥራ ማኅበራት ሱቆች በተጨማሪ በተለያዩ ቦታዎች በተለይም በጉለሌ፣ በአራት ኪሎ፣ በአየር ጤና፣ በኮልፌ አካባቢ እና በ18 ማዞርያ አካባቢ ለዶሮ እና እንቅላል የመሸጫ ቦታዎች መዘጋጀታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY