ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የባህር ዳር ከተማን ለማዘመን ደረጃውን የጠበቀ መዋቅራዊ የከተማ ፕላን አዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱን ገለጸ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ቡድን ከባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጀ ጋር ከመምከሩ ባሻገር ኢንስቲትዩቱ እየሠራቸው ያሉ ሥራዎችን ለቡድኑ አስተዋውቋል።
የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ በተቋሙ ውስጥ ያሉ አሠራሮችን ከማዘመን ባለፈ የባህር ዳር ከተማን ለማዘመን እየሠራ ነው ያሉት የባህር ዳር ዮኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኘ፤
ለአይ ሲ ቲ መሰረተ ልማት ትኩረት የሰጠ ደረጃውን የጠበቀ መዋቅራዊ የከተማ ፕላን በማዘጋጀት ወደ ሥራ መገባቱንም አስረድተዋል።