ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 5 ወራት ለ141 ሺኀ ወጣቶች የሥራ እድል መፈጠሩ ተፈጥሯል ተባለ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሓላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጊዜያት ወጣቱን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት ማከናወኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም 28 ሺኅ ወጣቶችን ለሚያሳትፍ የአረንጓዴ ልማት መረሀ-ግብር 2 ሚሊየን ብር መመደቡን አስረድተዋል።
የአዳነች አቤቤ አስተዳደር ይህን ይበል እንጂ በአዲስ አበባ ከተማ የሚከናወኑ የልማትም ሆነ የብድር ፕሮጀክቶች ላይ የአዲስ አበባ ወጣት ተጠቃሚ እንዳይሆን ውስጣዊ አሠራሮች እንቅፋት ሆነውበት መሰንበታቸውን መታዘብ ይቻላል።
በአዲስ አበቤ ላይ ግልጽ የሆነ ግፍ የፈጸመው የታከለ ኡማ አስተዳደርም ቢሆን የአዲስ አበባን ወጣት አግልሎ በከተማዋ ዙሪያ ለሚገኙ፣ ከአምቦ፣ አሩሲና ወለጋ ለመጡ ወጣቶች ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር ገንዘብ በማከፋፈል አዲስ አበቤው የበይ ተመልካች እንዲሆን ማድረጉም አይዘነጋም።