ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ የሴቶች ወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ (ሞዴስ) እና የሕጻናት ንጽህና መጠበቂያ (ዳይፐር) ምርቶች ላይ የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ አደረገች።
የገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከሆነ ከላይ የተጠቀሱትን የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ለምርታቸው በሚያስፈልጉና ከውጭ በሚያስገቧቸው የጥሬ እቃ ግብዓቶች ላይ የነበረው ታክስ እንዲነሳ ተላልፏል።
የሴቶችና የህጻናት ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ከውጭ ተመርተው ሲገቡም፤ ቀደም ሲል ተጥሎባቸው የነበረው የ30 በመቶ ከፍተኛ የታክስ ምጣኔ ተቀንሶ ወደ 10 በመቶ ብቻ እንዲሆን ተደሬጓል ነው የተባለው።
እነዚህ መሠረታዊ የንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በተለይም በወር አበባ ንጽህና መጠበቂያ ምርቶች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ለማስቻልና የሀገር ውስጥ አምራቾች እንዲበረታቱ በመታሰቡ ነው የቀረጥና የታክስ ማሻሻያ መደረጉ የተደረገው።