የህገ መንግሥት ማሻሻያ ጥያቄዎች በአግባቡ ሊታዮ ይገባል ተባለ

የህገ መንግሥት ማሻሻያ ጥያቄዎች በአግባቡ ሊታዮ ይገባል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የህገ መንግሥት ማሻሻያ ጥያቄዎች በአግባቡ ሊታዩ እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ።

15ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር የግምገማ መድረክ በአዳማ ተካሂዷል።
ህገ መንግሥቱ በፀደቀበት ቀን የምናከብረው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል፣ ሕዝቡ ስለ ህገ መንግሥት የተሻለ ግንዛቤ እንዲያገኝ እንደመልካም አጋጣሚ እንጠቀምበታለን በማለት በመድረኩ ንግግር ያደረጉት አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ ናቸው።
የህገ መንግሥት ማሻሻያ ጥያቄዎች በአግባቡ ሊታዩ ይገባል በማለት የተናገሩት አፈ ጉባኤዔው፣ በሀገሪቱ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ፍላጎት ማሻሻያ ሊደረግ እንደሚችልም ገልጸዋል።
ከማሻሻያ በፊት ዕውቀት አስፈላጊ ስለሆነ ስለ ህገ መንግሥቱ ግንዛቤ መፍጠር ወሳኝ ነው ያሉት አፈ ጉባዔ አደም ፋራህ፤ ከግንዛቤው ባለፈም ህገ መንግሥቱን ማክበር ግዴታ ነው ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY