ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በተለያዩ ጊዜያት በሀገር ክህደት ወንጀል ተጠርጥረው መያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸዉ አመራሮችና የጦር መኮንኖች መካከል በቁጥጥር ስር በዋሉት ምርመራ እየተካሄደ ነው ተባለ።
ከምርመራው ባሻገር በየጥሻውና በየጉድጓዱ የተደበቁትንም በማደን ላይ እንደሚገኝ የገለጸው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፤ እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ከፍተኛ መኮንኖች መካከል፤
1. ሜ/ጀኔራል ገ/መድህን ፈቃዱ ሀይሉ
2. ሜ/ጀኔራል ይዳው ገ/መድህን
3. ብ/ጀኔራል ገ/ህይወት ሲስኖስ ገብሩ
4. ብ/ጄኔራል ኢንሱ እጃጆ እራሾ
5. ብ/ጄኔራል ፍስሃ ገ/ስላሴ
6. ኮ/ል ደሳለኝ አበበ ተስፋዬ
7. ኮ/ል እያሱ ነጋሽ ተሰማ
8. ኮ/ል መብራቱ ተድላ ወ/ሚካኤል
9. ኮ/ል ባራኪ ጠማሎው ገብሩ
10. ኮ/ል ሀይላይ መዝገብ ማሾ
11. ኮ/ል ፍሰኃ ግደይ ወ/ማርያም
12. ሌ/ኮ/ል ሙዘይ ተሰማ ስዩም
13. ሌ/ኮ/ል ፍሰሃ በየነ ገ/ኪዳን
14. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ ወ/አረጋይ ገ/መስቀል
15. ሌ/ኮ/ል ምሩጽ በርሄ አበራ ላይ ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል ተብሏል።
በተያያዘ ዜና የመያዣ ትዕዛዝ ከወጣባቸው 81 የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተያዙት ዶ/ር አዲስአለም ባሌማ ብቻ መሆናቸውን ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።