ከኦነግ የተገፋው የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ምርጫ ቦርድን ከሰሰ

ከኦነግ የተገፋው የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ምርጫ ቦርድን ከሰሰ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከአርባ አመት በላይ በኦነግ ውስጥ የቆዮትና ለሁለት ዐሥርት አመታት ግንባሩን የመሩት ዳውድ ኢብሳና ባልደረቦቻቸው ምርጫ ቦርድን መክሰሳቸው ተሰማ።

በለውጡ ማግስት ወደ ሀገር ቤት የገባው ኦነግ በአቶ ዳውድ ኢብሳ መሪነት አነጋጋሪ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ቢሰነብትም ካለፈው አመት መገባደጃ ወዲህ በፓርቲው አመራሮች መካከል በተፈጠረ ውዝግብ፤ ሊቀ መንበሩ ዳዊት ኢብሳን ጨምሮ የተለያዮ አመራሮች ከሓላፊነት መታገዳቸው አይዘነጋም።
በህገ ወጥ መንገድ ከድርጅቱ ተገፍተናል ያለው የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ጉዳዮን ወደ ምርጫ ቦርድ መውሰዱን ተከትሎ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሁለቱን ወገኖች ክርክር ተመልክቶ ውሳኔ ሰጥቷል።
የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ግን ምርጫ ቦርድ እንደዋሸው ከመግለጹም ባሻገር የተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበለውም ይፋ አድርጓል።
በኦነግ ከፍተኛ አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ ምርጫ ቦርድ የአመራሮቹን ልዩነት ለመፍታትና የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ሁለቱም ቡድን የተካተቱበት ጠቅላላ ጉባዔ እንዲያካሂዱ  ታኅሳስ 9/2013 ውሳኔ ቢሰጥም፤ የእነ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ይህ ውሳኔ እኛ ላይ የተፈጸመ ክህደት ነው ሲል አጣጥሎታል። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቡድን ጉዳዮን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት ለመውሰድ መሰናዶውን እንዳጠናቀቅም አስታውቋል።

LEAVE A REPLY