የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር “እጅ አጥሮኛል” ሲል የድጋፍ ጥያቄ አቀረበ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር “እጅ አጥሮኛል” ሲል የድጋፍ ጥያቄ አቀረበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የፀጥታ ችግር፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ፣ የአንበጣ መንጋ ፣ ኮቪድ 19 እና ሌሎችም ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች የተከሰቱባቸውን ስፍራዎች ለማቋቋም የሰብዓዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ።

300 የበጎ ፈቃደኞች እና ሠራተኞችን እንዲሁም 100 አምቡላንሶችን በማሰማራት በቅርቡ በተከሰተው የአንበጣ መንጋ እና ከዚያ በኋላ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑትን ወገኖች ህይወት ለማዳን እና ኑሯቸውን መልሶ ለማቋቋም በንቃት እየሠራ መሆኑን የገለጸው ማኅበሩ አጋዦች እፈልጋለሁ ብሏል።
ላለፉት ሁለት ወራት የተከሰቱትን የፀጥታ ችግሮች ተከትሎ በትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እና ኦሮሚያ ክልሎች፣ በ30 ሚሊየን ብር ወጪ ከ200 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የህክምና፣ ምግብ፣ መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች አቅርቦቶች፣ የስነ-ልቦና ማህበራዊ እና መልሶ የማቋቋም ቤተሰብ የማገናኘት አገልግሎቶችን አካሂጃለሁ ያለው ማኅበሩ፤ በእነዚህ አካባቢዎች ተጨማሪ የጤና ማዕከል ተቋማትን እና የቀይ መስቀል ቅርንጫፎችን መጠገን እና መልሶ ለመገንባት እና ለተጠቀሱት ስፍራዎች እርዳታ ከ9 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስታውቋል።

LEAVE A REPLY