ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ እና የሀገር ሽማግሌዎች መማክርት ጥምረት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሃገር ሽማግሌዎች ጋር በአሶሳ ከተማ ተወያዮ።
የሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ÷ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኢትዮጵያውን አሻራ ያረፈበት የህዳሴው ግድብ መገኛ መሆኑን አስታውሶ፤
“ክልሉ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ማብሰሪያ ነው፤ በአካባቢው ተደጋጋሚ ግጭት እንዲነሳ የሚደረግበት ምክንያትም ይኸው ነው” ሲል ተደምጧል።
ፕሮጀክቱ ቢደናቀፍ የመጀመሪያ ተጎጂ የቅርብ ተጠቃሚ የሆነው የክልሉ ህዝብ እንደሆነም ማወቅ ያስፈልጋል ያለው ኃይሌ ገብረሥላሤ፤ የሃገር ሽማግሌዎች በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ሲዘዋወሩ በየቦታው የሚከሰቱ ግጭቱ ዘላቂ መፍትሔ እንዲኖረው አመራሮች በሓላፊነት እንዲሠሩ ጥያቄ እያቀረቡ መሆናቸውንም ይፋ አድርጓል።