ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ህወሓት ለከፍተኛ ፕሮፐጋንዳ ዘመቻ የሚጠቀምበት የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮን በበላይነት ስትመራ የነበረችው የህወሓት አባል እጇን ሰጠች።
የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ የነበራቸው ወ/ሮ ሊያ ካሳ ባለፉት ሁለት አመት እና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ በፌደራል መንግሥቱ እና በህወሓት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ የትግራይ ሕዝብን የሚያሳስቱ መረጃዎች እንዲተላለፉ ማድረጓ ይነገራል።
የህወሓት ከፍተኛ አመራሯ መከላከያ ሠራዊት መላ ትግራይን መቆጣጠሩን ተከትሎ ለሁለት ወራት ተሰውራ የነበረ ቢሆንም ዛሬ ከተደበቀችበት ወጥታ እጇን በሰላም ለመከላክያ ሠራዊት መስጠቷ ተረጋግጧል።