ስዮም መስፍን “ገርገልታ” በሚባለው ቦታ ከእነአጃቢዎቹ በመከላከያ ሠራዊት ተከቧል

ስዮም መስፍን “ገርገልታ” በሚባለው ቦታ ከእነአጃቢዎቹ በመከላከያ ሠራዊት ተከቧል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ የህወሓት ዋነኛ ፈላጭ ቆራጭ መሆኑ የሚነገርለት አቶ ስዮም መስፍን ያለበት አካባቢ ሙሉ ለሙሉ መከበቡ ታወቀ።

ገርአልታ ተብሎ በሚጠራውና ከመቀሌ ድንበር 18 ኪ/ሜትር፣  እንዲሁም ከመቀሌ ከተማ ደግሞ በግምት ከ 35 እስከ 40 ኪ/ሜትር በምትገኘው ስፍራ የተደበቀው ዋነኛ ተፈላጊ በመከላከያ ሠራዊት መከበቡን የመከላከያ ምንጮቻችን ነግረውናል።
 በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ በትግራይ ክልል የተለያዮ ገደላገደሎች፣ ጫካና ሸለቆዎች ውስጥ የመሸጉ ተጨማሪ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የከዱ ጀነራሎች እና ሻለቃዎች በቁጥጥር ሥር ለማዋል መከላከያ ሠራዊቱ ከፍተኛ አሰሳ እያደረገ መሆኑን ከታማኝ ምንጮች አረጋግጠናል።

LEAVE A REPLY