ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአማራ ክልል ሲሚንቶ ከፋብሪካዎች ተረክበው እንዲያቀርቡልኝ ከተመደቡ 37 የልማት ድርጅቶች እና ወኪሎች በትክክል ሓላፊነታቸውን እየተወጡ ያሉት ሠባቱ ብቻ ናቸው ሲል ገለጸ።
በሲሚንቶ ምርት ላይ የታየውን እጥረትና የዋጋ ንረት ተከትሎ መንግሥት ባለፈው ዓመት አዲስ የግብይት ሰንሰለት ቢዘረጋም ችግሩ አልተቀረፈም።
አዲሱ የግብይት ሰንሰለት 6 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርት በመረከብ ለቸርቻሪዎች እንዲያከፋፍሉ እና ራሳቸውም እንዲሸጡ የሚፈቅድ አሠራር ነው።
የልማት ድርጅቶቹ ራሳቸው ከሚመርጧቸው ወኪል አከፋፋዮች ጋር ተራ ገብተው ምርቱን የሚያነሱ ሲሆን፤
ወኪል አከፋፋዮቹን ጨምሮ በአጠቃላይ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ 93 የሲሚንቶ አቅራቢዎች እንዳሉ ታውቋል።
በክልሉ ከሲሚንቶ በተጨማሪ በብረት መሸጫ ዋጋ ላይም ከፍተኛ ጭማሪ መታየቱን የጠቆሙት አቶ አቢታ ይህን ተከትሎ የግንባታ ሥራዎች በከፍተኛ ሁኔታ መቀዛቀዙን ከመግለጻቸው ባሻገር፤ በክልሉ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ እስከ 600 ብር እየተሸጠ መሆኑንም አጋልጠዋል።