ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የይገባኛል ውዝግብ በተቀሰቀሰበት ድንበር አካባቢ ሱዳን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ ማድረግ መቀጠሏን እና ጦሯንም በከፍተኛ ሁኔታ እያስጠጋች መሆኗን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
“ሱዳን በድንበር አካባቢ በተጠናከረ ሁኔታ ጦሯን እያንቀሳቀሰች ነው” ያሉት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አምባሳየፈደር ዲና ሙፍቲ፤ ኢትዮጵያ ለሰላምና ለዲፕሎማሲያዊ መፍትኄ ቅድሚያ እንደምትሰጥ አስረድተዋል።
የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ጥሶ መግባቱን እና እየፈጸመችው ያሉ ሕገወጥ እንቅሰቃሴዎችን መታገሷ ከፍርሃትና ከመወላወል ጋር የተገናኘ አይደለም ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ላይ ለየት ያለ አቋም እያንጸባረቀች ያለችው ሱዳን በህዳሴው ግድብ ድርድር ላይም ተቃውሞ ማቅረቧንም ይፋ አድርጓል።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጦርነት አያስቸኩልም። አፍንጫህን የመታህን ወዲያውኑ አፍንጫውን ላትመታው ትችላለህ። ሌላ ጊዜ ግን አንገቱንም ልትቆርጠው ትችላለህ ሲሉም የሀገራቸውን አቋም በግልጽ አስታወቀዋል።