መከላከያ እርምጃ ወስጃለሁ ባለበት መተከል አሁንም 120 ንጹሃን ዜጎች ተገደሉ

መከላከያ እርምጃ ወስጃለሁ ባለበት መተከል አሁንም 120 ንጹሃን ዜጎች ተገደሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡ ከፍተኛ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት እና የሀገሪቱ የጦር ሹማምንቶች ይገኙበታል በተባለው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች አሁንም የሰዎች ህይወት እየጠፋ መሆኑ ተሰማ።

“ሰኞ እለት የመተከል ዞን አንድ ወረዳ በሆነችው ዳንጉር (ቀደም ሲል የጤና ባለሙያዎች የታፈኑበት አካባቢ) ማታ ላይ ሰው ተገድሏል። ከቻግኒ ወደ ከግልገል በለስ በሚሄድ ሕዝብ ማመላለሻ ላይ ጥቃት ተፈጽሞ አንድ ሰው ሞቶ ሦስት ቆስለዋል” ያሉ የመተከል ነዋሪ፤ “ማከስኞ ጠዋትም ወደ ግለግል በለስ በሚሄድ መኪና ኤዲዳ ወይንም ቁጥር 2 በምትባል ቦታ ላይ አንድ ሰው ተገድሏል። ሁለት ሰዎች ቆስለው አሁን ሕክምና ላይ ይገኛሉ” ብለዋል።
በተመሳሳይ በድባጤ ወረዳ ዳለቲ ቀበሌ ላይ እጅግ በርከታ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ በርካታ ቤቶች እየተቃጠሉ መሆኑን የአከባቢው ነዋሪ የሆኑ የአይን ምሥክሮች ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን አስረድተዋል።
ሰኞ ዕለት በጉባ ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 15 መድረሱን ከከተማዋ ነዋሪዎች የተናገሩ ሲሆን ከዘሬ ጠዋት ጀምሮ በድባጤ ወረዳ በተፈጸመ አሰቃቂ ጥቃት ከ120 በላይ የሆኑ ህፃናትና እናቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈው መገደላቸውን  ለመንግሥት መገናኛ ብዙሀንና ለቪኦኤ የአይን ምስክሮቹ  ይፋ አደርገዋል።
ሰሞኑን በርካታ ንጹሃን ዜጎችን የቀጠፈውን ጥቃት አስመልክቶ ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት የክልሉ የኮምዩኒኬኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት የሚችለው የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

LEAVE A REPLY