በትግራይ ክልል በቀጣዮቹ ሳምንታት ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው

በትግራይ ክልል በቀጣዮቹ ሳምንታት ትምህርት ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ ሥራዎች እየተከናወኑ ተሰማ።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ በክልሉ የተደረገውን የህግ ማስከበር ተከትሎ መቀሌና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ያስመረቁ መሆኑን አስታውሰው፤ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 07/2013 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት እንዲጀምሩ መደረጉን ገልጸዋል።
 በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በህግ ማስከበር ወቅት የደረሰውን ጉዳት  የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ምልከታ ያደረጉ ሲሆን፤ በወቅቱ ከተማሪዎች እና የዩኒቨርሰቲዉ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY