የከተራ እና ጥምቀት በዓልን በሰላም ለማክበር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በቂ ፀጥታ ተመድቧል

የከተራ እና ጥምቀት በዓልን በሰላም ለማክበር በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል በቂ ፀጥታ ተመድቧል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበሩ የፌዴራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ማደረጋቸው ተሰማ።

ኢትዮጵያ በዓለም ዐቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንደኛው  የጥምቀት በዓል መሆኑ አይዘነጋም።
በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ሰ የበፌዴራል፣ የክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽኖች እንዲሁም የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት በቂ ዝግጅት በማድረግ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የገለጸዉ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ፤ ሕብረተሰቡም ለየት ያሉ ነገሮችን ሲመለከት ጥቆማ እንዲያደርግ አሳስቧል።
  የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር ለማድረግ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በርካታ የፀጥታ አካላት ማሰማራቱንም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY