ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለሥልጣን የላዳ ታክሲዎችን በዘመናዊ መኪኖች ለመቀየር ከታክሲ ማህበሩ ጋር ውይይት አደረገ።
የከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን መንግሥቱ ማኅበሩ የላዳ ታክሲዎችን በዘመናዊ መኪኖች እንዲቀይር መንግሥት ከቀረጥ ነጻ እንዲያስገቡ ከመፍቀዱ ባሻገር የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
መኪኖችን ከቀረጥ ነፃ ማስገባት የተፈቀደላቸው ማህበራት የቀረጥ ነፃ ጊዜው ረጅም ጊዜ የሚቆይ ባለመሆኑ በጊዜው እንዲጠቀሙ መልእክት ከመተላለፉ ባሻገር፤ የላዳ ታክሲ ባለንብረቶች ዘመናዊ ታክሲዎችን ለመውሰድ በአምስት ባንኮች የጀመሩትን ቁጠባ እና የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለባቸውም ተነግሯቸዋል።