ለጠቅላላ ሐኪምች የተሰጠው ፈተና ጥያቄ ተሰርቆ መውጣቱ እያነጋገረ ነው

ለጠቅላላ ሐኪምች የተሰጠው ፈተና ጥያቄ ተሰርቆ መውጣቱ እያነጋገረ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በኢትዮጵያ ለጠቅላላ ሐኪሞች የተሰጠው ፈተና ጥያቄ አስቀድሞ መውጣቱ አነጋጋሪ ሆነ።

ከቀናት በፊት ለጠቅላላ ሐኪሞች የተሰጠው የብሔራዊ ስፔሻሊስት ፈተና ዘርፈ ብዙ ችግር አለበት ያለው የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማህበር (ኢጤሙተማ) ነው።
ጤና ሚኒስትር በየዓመቱ ከ 1 ሺሕ ለሚበልጡ ሐኪሞች ብሔራዊ የስፔሻሊስት ፈተና በመስጠት ለከፍተኛ የሕክምና ለ ዩኒቨርሲዎች በመላክ እንደሚያስተምር ያስታወሰው ማኅበሩ፤ በዚህ ዓመት በተሰጠው የብሔራዊ ስፔሻሊስት ፈተና ላይ ግን በርካታ ተፈታኝ ተማሪዎች ቅሬታ አላቸው ብሏል።
 የኢትዮጵያ ጤና ሙያ ተማሪዎች ማህበር (ኢጤሙተማ) ፕሬዝዳንት ዶክተር ሲሳይ አበበ ይህ ፈተና ከመሰጠቱ አስቀድሞ 20 ጥያቄዎች ” ለኢትዮጵያ ተፈታኝ ሐኪሞች” በሚል በቴሌግራም መለቀቁንም አጋልጠዋል።

LEAVE A REPLY