ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባለፉት ወራት በተለያዮ ጉዳዮች ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት አቶ ልደቱ አያሌው ፍርድ ቤት ቀረቡ።
አቶ ልደቱ ህገወጥ መሳሪያ ይዞ መገኘት በሚል ተከሰው የነበረ ቢሆንም፤ መሳሪያው በሌላ ህገ ወጥ መንገድ ያልተገኘ እና የመንግሥት ንብረት ስለመሆኑ በፖሊስም በዐቃቢ ህግም መረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አያስቀጣም ብሏል።
ከዚህ በተጨማሪም መሳሪያውን የታጠቁት “ያለፈቃድ መሳሪያ ይዞ መገኘት ወንጀል” መሆኑን የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ ከመውጣቱ ከብዙ አመታት በፊት እና የፓርማ አባል በነበረበት ወቅት መሆኑ ስለተረጋገጠ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዳሰናበታቸው ታውቋል።
ልደቱ አያሌውን ፍርድ ቤቱ ነፃ ይበላቸው እንጂ ከወራት በፊት እርሳቸውም በዚህ ፍርድ ቤት ቀርበው እንደመሰከሩት እና ፖሊስም እንዳስታወቀው መሳሪያው በመጥፎነቱ የሚታወቀው የደህንነቱ ኢሳያስ ወልደ ጊዮርጊስ መሆኑ ሲያወዛግብ ቆይቷል።