ምርጫ ቦርድ የመቀመጫ እና የምርጫ ክልል ለውጦችን አልቀበልም አለ

ምርጫ ቦርድ የመቀመጫ እና የምርጫ ክልል ለውጦችን አልቀበልም አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘ የክልል እና የከተማ መስተዳድሮች የመቀመጫ እንዲሁም የምርጫ ክልል ለውጦች እንደማይቀበል ገለጸ።

የመቀመጫ እና የምርጫ ክልል ለውጦችን በማከናወን በዚያ መሠረት ምርጫ እንዲፈጸምላቸው ከጠየቁ ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል እንዲሁም የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል።
የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 ዓ.ም አንቀጽ 7(4) መሠረት መቀመጫ ለመቀየር የሚሰጡት ውሳኔ ከእጩዎች ምዝገባ 6 ወራት አስቀድሞ መሆን እንደሚኖርበት ይደነግጋል ያለው ቦርዱ በዚህ ምክንያት ጥያቄዎቹን አላስተናግድም፣ ምርጫውም አስቀድሞ በወጣለት የጊዜ ሰሌዳ አማካይነት ይካሄዳል ብሏል።

LEAVE A REPLY