በአዲስ አበባ 25 ያልተፈቀዱ በዓላት ምክንያት ትምህርት ቤቶች ይዘጋሉ ተባለ

በአዲስ አበባ 25 ያልተፈቀዱ በዓላት ምክንያት ትምህርት ቤቶች ይዘጋሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በአዲስ አበባ እስከ 25 የሚደርሱ ያልተፈቀዱ በዓላት በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጭምር እየተከበሩ መሆናቸው ተሰማ።

በዓላቱን ተገን በማድረግ ገቢ የሚሰበስቡ ትምህርት ቤቶች እና መምህራን መኖራቸውን የገለጸው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፤ በትምህርት ቤቶች የሚከበሩ በዓላት በከፍተኛ ሁኔታ የትምህርት ሥራውን እያወኩብኝ ነው ሲልም ቅሬታውን አሰምቷል።

ጉዳዮ ከሚመለከታቸው የትምህርት ባለጉዳዮች ጋር ዛሬ የስምምነት ፊርማ በተከናወነበት ወቅት በተሰጠ ማብራሪያ፤ በትምህርት ቤቶች የሚከበሩ በዓላት የተማሪ ቤቶችን ሀብት እና ንብረት ከማውደም ባለፈ፤ የተማሪዎችን እና የመምህራንን ሰብዓዊ መብቶች እየጣሱ ናቸው ብሏል።
በመንግሥት ከተፈቀዱና ትምህርት እንዲዘጋ ከሚያደርጉ ብሔራዊ በዓላት ውጪ፤ እስከ 25 የሚደርሱ ያልተፈቀዱ በዓላት በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጭምር እየተከበሩ ይገኛሉ ያለው ቢሮው፤ ይህን የሚከለክል መመሪያ ቢወጣም፤ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች እና መምህራን ትምህርታዊ ጉብኝቶችን ተገን አድርገው የበዓላት ዝግጅቶችን ለገንዘብ ማግኛነት እየተጠቀሟቸው እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY