በአዲስ አበባ በየመንደሩ የሚገኙ ሱቆች እና መደብሮች እየተዘጉ ነው

በአዲስ አበባ በየመንደሩ የሚገኙ ሱቆች እና መደብሮች እየተዘጉ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከወሰን ውጪ አልፈዋል፤ መንገድ ዘግተዋል በተባሉ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዮ መንደሮች በሚገኙ ሱቆች እና መደብሮች ላይ ሰሞኑን እርምጃ እየተወሰደ ነው ተባለ።

የከተማዋ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በጎዳና ላይ በህገ-ወጥ መንገድ እየሰሩ ነው የተባሉ የመንገድ ላይ ሻጮችም ሰሞኑን በከተማዋ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የሚደርስባቸው ማሳደድና ሩጫ መበራከቱ እየተነገረ ነው።
“ጽ/ቤቱ እየወሰደ ያለው እርምጃ እኛ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው፣ ተደራጅተን እንድንሠራ ይፈቀድልን ስንል የሚሰማን አጣን” በሚል በጎዳና ንግድ ላይ የተሠማሩ ወገኖች ቅሬታ  አቅርበዋል።
በተለያዮ የከተማዋ መንደሮች ውስጥ ያሉ ሱቆች እና መደብሮች “የፀሐይ መከላከያ” በሚል በሚወጠሩ ላስቲኮች እና ቆርቆሮዎች አማካይነት ከፍተኛ የመስፋፋት እንቅስቃሴ እየታየ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን የማስከበሩ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል።

LEAVE A REPLY