በታንዛንያ እስር ቤቶች የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተባለ

በታንዛንያ እስር ቤቶች የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በታንዛንያ እስር ቤቶች የነበሩ 80 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ በታንዛንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ ይፋ አደረጉ።

በእስር ቤቶቹ የሚገኙ 1 ሺኅ 800 ኢትዮጵያውያንን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ያሉት አምባሳደሩ፤ በዳሬሰላም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሕዳር ወር 2013 ዓ.ም በሞሮጎሮ፣ ታንጋ፣ ፕዋኒና ባጋሞዮ ግዛቶች ባደረገው ምልከታ ከ1 ሺኅ በላይ ኢትዮጵያዊያን በእስር ቤቶች እንዳሉ ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።
 በአራቱ ግዛቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይቅርታ ተደርጎላቸው እንዲፈቱ እና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከታንዛንያ የኢሚግሬሽንና ማረሚያ ቤት ተቋም ጋር ሲነጋገር መቆየቱን፣ ተቋሙም በጎ ምላሽ መስጠቱን አምባሳደሩ ተናግረዋል።
በታንዛንያ የሚገኘው የዓለም ዐቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) ቢሮ ከእስር የተለቀቁ 80 ኢትዮጵያዊያን በሁለት ሳምንት ጊዜ ወስጥ ወደ አገራቸው የሚመለሱበትን ገንዘብ እንደሚሸፍንም ከወዲሁ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY