በቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ማብራሪያ ተሰጠ

በቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለወቅታዊ የሀገሪቱ ሁኔታ ማብራሪያ ተሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ቻይና በትምህርት ላይ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር በትግራይ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ፣  በኢትዮጵያ ሱዳን የድንበር ግጭት እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ውይይት ተካሄደ።

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በትግራይ እየተካሄደ ባለው የህግ ማስከበር ሂደት መንግስት በአሁኑ ወቅት በትኩረት የሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብና የፈራረሱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ እየገ ነባ መሆኑን ጠቁመው፤ ድጋፍ ለሚሹ 2.5 ሚሊዮን ወገኖች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ አቅርቦቶች ለማዳረስ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የቻይና መንግሥት ከጅምሩ ጉዳዩ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ መሆኑን እና የውጭ አካላት ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ አይደለም በሚለው አቋሙ የጸና መሆኑን  ያስታወሱት አምባሳደር ተሾመ፤ የቻይና መንግሥት በዓለም ዐቀፍ ተቋማት በኩል ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማሳደግ እየሠራ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ግጭት  ከቅኝ ግዛት የሚመዘዝ  ነው ያሉት አምባሳደሩ፤ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር በወረቀት ላይ ካልሆነ መሬት ላይ የተካለለ ባለመሆኑ ችግሮች ሲከሰቱ መቆየቱን ከማስታወሳቸው ባሻገር፤ የወቅቱ መንግሥታት የተለያዩ ስምምነቶችና ውይይቶች ሲያካሂዱ መቆየታቸውን፣ እ.ኤ.አ በ1902 ሀገራቱ የደረሱት ስምምነት መኖሩን፣ በተለይም በ1972 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚታወቅ የሰነድ ልውውጥ ስምምነት ሁለቱ ሀገራት በያዙት ቦታ እንዲቆዩ መደረጉንም ለኢትዮጵያውያኑ ተማሪዎች አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY