750 የህወሓት ልዮ ኃይል፣ ፖሊስ እና ሚሊሺያ አባላት ዳግም ወደ ሕብረተሰቡ ሊቀላቀሉ...

750 የህወሓት ልዮ ኃይል፣ ፖሊስ እና ሚሊሺያ አባላት ዳግም ወደ ሕብረተሰቡ ሊቀላቀሉ ነው

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ቁጥራቸው ከሠባት መቶ ሃምሳ በላይ የሆኑ የቀድሞው የህወሓት ልዮ ኃይል፣ ፖሊስ እና ሚሊሺያ አባላት ወደ ከስልጠና በኋላ ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጅቱ ተጠናቋል ተባለ።

ለመከላከያ እጃቸውን ከሰጡ የጁንታው ጦር አባላት መካከል በአፋር ክልል አዋሽ አርባ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል 764 የቀድሞ የህወሃት ልዩ ኃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ድጋፍ የተሃድሶ ስልጠና ሲሰጣቸው የበረውን ስልጠና አጠናቀዋል።
አብዛኛው ሰልጣኞች ከግብርና ሥራ ላይ ተገደው ወደ ውጊያ የተሰማሩ አርሶአደሮች በመሆናቸው፣ ከፖሊስና ሚሊሻ አባላቱ ም በርካቶቹ በጽንፈኛው የህወሃት ቡድን ጠባብነትና ተገፊነት እኩይ አስተሳስቦች ሰለባ በመሆናቸው የተሃድሶ ስልጠና መስጠቱ በመንግሥት በኩል አስፈላጊነቱ ታምኖበታል።
በቀጣይም ወደ የአካባቢያቸው ተመልሰው ከሕብረተሰቡ ጋር ተቀላቅለው መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ መታሰቡን ያመላከተው ዜና፤ ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ሲያጠናቅቁ የተለየ ሁኔታ ጥፋት የፈጸሙ ካልሆኑ በስተቀር ቀሪዎቹ ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱና በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲደገፉ ይደረጋል ብሏል።

LEAVE A REPLY