ለኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ድንበር ጥበቃ አውሮፓ ሕብረት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን...

ለኢትዮጵያ እና ሱዳን የጋራ ድንበር ጥበቃ አውሮፓ ሕብረት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዮሮ ድጋፍ አደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአውሮፓ ህብረት ለቦማ-ጋምቤላ የብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ፕሮጀክት 4 ነጥብ 4 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ተሰማ።

ሕብረቱ የምስራቅ አፍሪካ በይን መንግሥታት /ኢጋድ/ በደቡብ ሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ የአካባቢ ጥበቃ ሥራን ለመደገፍ ያለመ  እርዳታ መስጠቱ ከወዲሁ እየተነገረለት ነው።
ስምምነቱን የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ እና በጅቡቲ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ አምባሳደር ኤይዳን ኦሃራ ተፈርመዋል፡፡
ቦማ-ጋምቤላ መልክዓ ምድር በደቡብ ሱዳን እና በኢትዮጵያ ድንበር የሚገኝ ሲሆን፤ የተለያዩ የዱር እንስሳት ፣ እንዲሁም ብርቅዬ እና የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ዝርያዎችን እንደያዘ ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY