በአዲስ አበባ 323 ባለቤት አልባ ሕንፃዎች ተገኙ

በአዲስ አበባ 323 ባለቤት አልባ ሕንፃዎች ተገኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ ባለቤት አልባ 323 ሕንጻዎች መገኘታቸውን ከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።

የሕንፃዎቹ ባለቤት እኔነኝ ብሎ የቀረበ የለም ያሉት የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በተደረገ ጥናት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ከተገነቡት ከእነዚህ ሕንፃዎች መካከል 58ቱ ተጠናቀው እየተከራዩ ያሉ መሆናቸውንም አጋልጠዋል።
264 ሕንፃዎች ግንባታቸው ተጀምሮ፣ በተለይ ከለውጡ በኋላ ሳይጠናቀቁ ግንባታቸው የቆሙ ናቸው ያሉት ከንቲባዋ፤ ሕንፃዎቹ ሲገነቡ ምንም ዓይነት የግንባታ ፈቃድ ያልወሰዱ እና እያንዳንዱ ሕንፃ ከ500 ካሬ ሜትር በላይ ቦታ የያዘ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
በጥናት የተገኙት ባለቤት አልባ ሕንፃዎች የያዙት አጠዋላይ የቦታ ስፋት 229,556 ካሬ ሜትር እንደሆነም ከመግለጫው መረዳት ችለናል።
ም/ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ውሰጥ የሚገኙ በተለያዩ ህገወጥ አሰራር የተያዙ፣ ባለቤት አልባ፣ ከህግ ውጭ የተላለፉ፣ ተሰበረው የተገባባቸው…. ህንጻዎች፣ ቤቶች እና ኮንዶሚኒየሞችን ዝርዝር አብራርተዋል። በዚህም መሰረት –

– 332 ባለቤት የሌላቸው ህንጻዎች ተገኝተዋል

– 15ሺ 891 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ውሰጥ ግለሰባች ያለምንም ማስረጃ ይኖራሉ

– 32ሺ እጣ ሳይወጣላቸው ቤቶች

– 7723 የቀበሌ ቤት ማስረጃ የሌላቸው

– 4530 ኮንዶሚኒየም ቤቶች አንድ ወቅት ላይ ሰው ኖረውባቸው አሁን ለቀው ጠፍተዋል

– 424 ኮንዶምንየም ማንም የሚኖርበት ሰለሌለ ግለሰቦች ሰብረው የገቡባቸው

– 265 የቀበሌ ቤቶች ለ3ኛ ወገን የተላለፉ

– 1243 የራሳቸው ኮንዶሚኒየም እያላቸው የቀበሌ ቤቶች የሚኖሩ ——-

– 1243 የቀበሌ የታሸጉ ቤቶች
– 180 የቀበሌ ቤቶች ጠፍተው በጥናት መገኘታቸው ተገለፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY