አራት ዲፕሎማቶች የትግራይ ሁኔታ አሳስቦናል አሉ

አራት ዲፕሎማቶች የትግራይ ሁኔታ አሳስቦናል አሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአውሮፓ ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በትግራይ ያለው ሁኔታ ያሰጋናል አሉ።

በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በትግራይ ክልል እየተወሰደ ያለው ሕግ የማስከበር እርምጃ ያሰጋናል ካሉት መካከል  በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ዲፕሎማቶች ይገኙበታል።

የቀድሞ አምባሳደሮቹ ጽኑ ስጋታቸውን ያንጸባረቁት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ሲሆን፤ አምባሳደሮቹ በትግራይ ክልል የተከሰተው ግጭት እንዳሳሰባቸውም ዘወትር ረቡዕ እና እሁድ ለሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ በላኩት ይፋ ደብዳቤ ላይ አስታውቀዋል።

አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ ኡሬሊያ ብራዜለ፣ ቪኪ ሃድልስተን እና ፓርቲሺያ ሃስላች እንደ አውሮጳዊያን አቆጣጠር ከ1996 እስከ 2016 ባሉት ዓመታት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉ ናቸው።

በተመሳሳይ የአውሮፓ ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተወካዮች በትግራይ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

LEAVE A REPLY