የጃዋር ቤተሰቦች በለበሱት ቢጫ ልብስ ምክንያት የዛሬው ችሎት ተቋረጠ

የጃዋር ቤተሰቦች በለበሱት ቢጫ ልብስ ምክንያት የዛሬው ችሎት ተቋረጠ

A high-profile Ethiopian activist, Jawar Mohammed is photographed during an interview, in Addis Ababa on October 25, 2019. - A high-profile Ethiopian activist at the centre of violence that left 16 people dead this week has accused Prime Minister Abiy Ahmed of acting like a dictator and said he might challenge him in elections planned for next year. (Photo by Michael Tewelde / AFP) (Photo by MICHAEL TEWELDE/AFP via Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብርና ሕገመንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ የተከሳሾችን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሊቀበል ቀጠሮ ቢይዝም ሆን ብለው ውዝግብ ለመፍጠር በመጡት የጃዋር መሐመድ ቤተሰቦች እና የቅርብ ዘመዶቹ አለባበስ ምክንያት ችሎቱ ሊቋረጥ ችሏል።

የተከሳሾቹን የፍርድ ሂደት ለመከታተል ቢጫ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤት የተገኙ ሰዎች ወደ ፍርድ ቤቱ እንዳይገቡ በፖሊስ መከልከላቸውን ተከትሎ ተከሳሾች እና ጠበቆች ባሰሙት አቤቱታ መሠረት ነው ችሎቱ ሊቋረጥ የቻለው።

” ሰዎች ቢጫ ቀለም ያለው ልብስ በመልበሳቸው ወደ ፍርድ ቤት እንዳይገቡ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ ቢጫ ልብስ በመልበሳቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ አሉ” ሲሉ ቅሬታቸውን ለፍርድ ቤት ያቀረቡት ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነ (ቦረና) በዚህ ሁኔታ ቃላችንን መስጠት አንፈልግም ብለዋል።

ተከሳሾች በማረሚያ ቤት እና ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚለብሱትን ባለ ቢጫ ቀለም ቱታ በመልበስ አጋርነታችንን ለማሳየት ነው የመጣነው ያሉ የተለያዮ የጃዋር መሐመድ ቤተሰቦች፣ የቅርብ ዘመዶች እና ጥቂት ደጋፊዎች ፍርድ ቤቱ አካባቢ ግርግር ለመፍጠር መሞከራቸውን ተከትሎ በጸጥታ ኃይሎች ሲያዙ ለማየት ተችሏል።

LEAVE A REPLY