ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የራሱንና የተጠሪ ተቋማቱን በአንድ ቦታ ለማሰባሰብ የሚያስችል የጋራ ሕንጻ ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።
ሁለት ሄክታር መሬት ከጉለሌ ክፍለ ከተማ በዚህ ሳምንት መጀመርያ ሰኞ ጥር 10 2013 መረከቡን ያሴታወቀው ተቋሙ፤ ግንባታውም በአጭር ጊዜ እውን ይሆናል ብሏል።
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ደሳለኝ ሳሙኤል ከጉለሌ ክፍለ ከተማ በተሰጠው ሁለት ሄክታር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ መገኘቱን ተከትሎ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት አፈሩ በባለሙያ ተመርምሮ እና መሸከም የሚችለው የሕንጻ አይነት በሕንጻ ዲዛይን ባለሙያዎች ተጠንቶ ፣ የሕንጻ ዲዛይን በማወዳደር ግንባታው ይጀመራል ብለዋል።