የወጋገን ባንክ የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አባይ መሀሪ ተከሰሱ

የወጋገን ባንክ የቀድሞ ፕሬዘዳንት አቶ አባይ መሀሪ ተከሰሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የትህነግ አባላት ያቋሙት እና አብዛኛውን ሼር የተቆጣጠሩበት ወጋገን ባንክ የቀድሞ ፕሬዘዳንት ታሰሩ።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዘዳንቱን ጨምሮ ስምንት የባንኩ የሥራ ሃላፊዎች የሙስና ወንጀል ክስ መስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል።
የቀድሞ ወጋገን ባንክ ፕሬዘዳንት ግንባታ ባልተካሄደበት ይዞታ ከ63 ሚሊየን ብር በላይ በማበደር ተጠርጥረዋል።
በዚህ መሠረት ጥር 19 ቀን 2013 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ፀረ ሙስና ችሎት የተከሳሾችን የተመለከተ ሲሆን፤  የወጋገን ባንክ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ አባይ መሃሪም በችሎቱን ተገኝተዋል።
አንደኛ ተከሳሽ አቶ አባይ መሃሪ “ቋሚ አደራሻ እያለን በፌደራል ፖሊስ ሳንጠራ እንደ ማንኛውም ሰው በመገናኛ ብዙኃን ሰምተን በፍቃደኝነት መጥተናል” ሲሉ በጠበቃቸው በኩል ለችሎቱ አመጣጣቸውን አስረድተዋል፡፡
በጡረታ ነው የምተዳደረው ያሉት አቶ አባይ መሀሪ  ጡረታቸው እንደታገደባቸው እና ለችሎቱ የዋስትና ሊከበርላቸው እንደሚገባ በመግለጽ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱ በጉዳዮ ላይ ብይን ለመስጠት ለጥር 25፣2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል። እስከዛ ድረስም የቀድሞ የወጋገን ባንክ ፕሬዘዳንት አቶ አባይ መሃሪ እስከዛው ባሉበት እንዲቆዩ ሲል አዟል፡፡

LEAVE A REPLY