በትግራይ ሲዋጉ እና ሲያዋጉ የነበሩ 18 መኮንኖች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በትግራይ ሲዋጉ እና ሲያዋጉ የነበሩ 18 መኮንኖች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ከጁንታው ታጣቂ  ኃይል ጋር ተሰልፈው ከመቀሌ እስከ ቆላ ተንቤን ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በመከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ጸጥታ ኃይሎች የጋራ አሰሳና ፍተሻ ስራ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል መሀመድ ተሰማ ፤ በቀጥጥር ሥር ከዋሉት መኮንኖች መካከል ዘጠኙ የሙሉ ኮሎኔል ማዕረግ፤ ሠባቱ የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ ያላቸው፣ ሁለቱ  የፖሊስ ኮማንደሮች መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከጁንታው የጥፋት ቡድን ጋር በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የተሰለፉ ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ  እጃቸውን ለመንግሥት እንዲሰጡ ጀነራሉ ዳግም መልዕክት አስተላልፈዋል

LEAVE A REPLY