ህገ ወጥ መሬት እና ቤቶቹን ለነዋሪዎች እንደሚያከፋፍል አ/አ መስተዳድር ገለጸ

ህገ ወጥ መሬት እና ቤቶቹን ለነዋሪዎች እንደሚያከፋፍል አ/አ መስተዳድር ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በተደረገ ጥናት ተገኙ የተባሉትን ህገ ወጥ መሬቶች እና ቤቶች ለነዋሪዎች እንደሚያከፋፍል ከተማ አስተዳደሩ ገለጸ።

በከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ መአረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጃንጥራር አባይ ፤ በጥናቱ የተገኙት መሬት እና ቤቶች ወደ መንግሥት ካዝና ገቢ ተደርገው በትክክል የቤት ችግር ላለባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ይከፋፈላሉ ሲሉ ተደምጠዋል።
ህገወጥ የቤትና የመሬት ዝርፊያ ሲፈጸም የተባበሩ እና ኃላፊነታቸውን ያልተወጡ አመራሮች በህግ በመጠየቅ ላይ ናቸው ያሉት ጃንጥራር፤ በመሬት እና መኖሪያ ቤቶቹ ክፍፍል ላይ ዳግም ስህተት እንዳይፈጠር እንተጋለን ብለዋል።

LEAVE A REPLY