ህወሓት ላይመለስ መደምሰሱን መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ

ህወሓት ላይመለስ መደምሰሱን መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የህወሓት የጥፋት ቡድን ላይመለስ መደምሰሱን የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ገለጹ።

የመከላከያ ሚኒስትሩ በህወሓት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በህግ ማስከበርና ህልውና ዘመቻው ወቅት ዕጅ ሰጥተው በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ሥልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙትን የትግራይ ክልል  ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላትን  አወያይተዋል።።
 ”ደም መጣጩ ቡድን እናንተን እሳት ውስጥ ማግዶ ተደምስሷል” ያሉት ሚኒስትሩ፤ ትህነግ ለግል ጥቅሙ እና ለሥልጣን ጥማቱ ሲል እኩይ ተግባራትን በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጽሞ ላይመለስ ተወግዷል ሲሉም አብራርተዋል፡፡
እጅ ሰጥተው በደቡብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ላይ ከሚገኙት 764 ዜጎች ጋር በተደረገው ውይይት ላይ፤ የመከላከያ ሚኒስትሩ ፣ ሌ/ጀ ሀሰን ኢብራሂምን ጨምሮ ሌሎች ጀነራል መኮንኖች እና የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሓላፊ ነቢዩ ስሁል ተገኝተዋል።

LEAVE A REPLY