ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሒም ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በተመሳሳይ የክስ መዝገብ የቀድሞ የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባልና የትራንስፖርት ሚኒስትር ድኤታ የነበሩት ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሄርም ዛሬ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ነበር፡፡
መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው 14 የምርመራ ቀናት የከወናቸውን የምርመራ ሥራዎች ለችሎት ሲያብራራ ተጠርጣሪዎቹ፤ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በመከላከያ ሠራዊት አባላት ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ከ2010 ጀምሮ ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ብሄርና ሃይማኖት መሰረት ያደረጉ ግጭቶች እንዲነሱ እገዛ ሲያደርጉ ነበር ሲል አስረድቷል።
ለዚህ ማስረጃ 10 የሰው ምስክሮች ቃለ መቀበሉን ለፍርድ ቤቱ ጠቁሞ፤ በጦርነቱ  ምክንያት  በክልሉ  የደረሰውን ጉዳት  በተመለከተ  ከደህንነት  መ/ቤት ከኤርፖርቶች  ድርጅቶችና  ሌሎችም  ተቋማት  ማስረጃ  ለማሰባሰብ ወደ  ክልሉ  የምርመራ  ቡድን  ስለተላከ  ተጨማሪ  14 የምርመራ  ቀናት በጠየቀው መሠረት በችሎቱ ተፈቅዶለታል።

LEAVE A REPLY