በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ነው ተባለ

በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሠራ እንደሚገኝ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታወቀ።

“በኤርትራ ስደተኞች ላይ ችግር እንደደረሰ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ እውነታውን ያላገናዘበ ነው” ያለው ኤጀንሲው፤ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎችን መጎብኘታቸውንም ይፋ አድርጓል።
በጉብኝቱ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን፣ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ከተመድ ልዑካን ቡድን ጋር በስፍራው መገኘታቸው ተረጋግጧል።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች ነው።

LEAVE A REPLY