21 ሺኅ መኖሪያ ቤቶች ከነገ ጀምሮ ለ97 ተመዝጋቢዎች በዕጣ ይከፋፈላል ተባለ

21 ሺኅ መኖሪያ ቤቶች ከነገ ጀምሮ ለ97 ተመዝጋቢዎች በዕጣ ይከፋፈላል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋዊ ትዊተር ገጻቸው፤ በሕገወጥ መንገድ የተያዙና ዝግ ቤቶች ለተመዝጋቢዎች እንደሚሰጥ አሰታወቁ።

በዚህም መሰረት 21 ሺህ 695 የኮንዶሚኒየም ቤቶች ለ1997 ዓ.ም ተመዝጋቢዎች እና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ ይተላለፋል ተብሏል። 

በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች የከተማ አስተዳደሩ እንዲወርስ እና በግልፅ ጨረታ እንዲሸጡ ካቢኔው ውሳኔ አሳልፏል።

የቀበሌ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወጥቶላቸው ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ የከተማው ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ ንግድ ቤቶቹም ቢሆኑ በህገ-ወጥነት ከያዙት ቤቶች አስለቅቆ ለሥራ አጥ ወጣቶች ከነገ ጀምሮ በእጣ እንዲከፋፈል ተወስኗል።

LEAVE A REPLY