ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ላደረጉ በድሬዳዋ እና አካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት የእውቅናና የምስጋና ሽልማት አበረከተች፡፡
ከዐሥር ቀን በፊት የተከበረው ጥምቀትን ጨምሮ ሌሎች ሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት ያለ ፀጥታ ችግር እንዲከበር ላደረጉ የፀጥታ አካላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የምስጋናና የእውቅና ሽልማት መስጠቱ ተሰምቷል።
የምስራቅ ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የምስራቅ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ አባላት፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህና ፀጥታ ህግ ጉዳዮች ቢሮ ናቸው ተሸላሚዎቹ።
በዕውቅና መርሀ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ተገኝተዋል።