ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን አስተዳደር ለመደገፍ የተጠሩ ሰልፎች ዛሬም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች መቀጠላቸው ታውቋል።
ሆለታ፣ መቱ፣ ፊቼ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ሰንዳፋ በኬ ዛሬ የድጋፍ ሰልፉ ከተካሄደባቸው የክልሉ አካባቢዎች መካከል ለአብነት ይጠቀሳሉ።
በቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ አምቦ፣ እንዲሁም ምስራቅ ሃረርጌ እና ጉጂ ዞንም ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን፤ የሰልፎቹ ዋነኛ ዓላማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ አንስቶ ለሰጠው ጠንካራ አመራር ምስጋና ማቅረብ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ትናንትም ተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፎች በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መካሄዳቸው አይዘነጋም፡፡