በ19 ሚሊዮን ዶላር ብድር የተገዙት 49 የወደብ ማሽኖች ኢትዮጵያ ገቡ

በ19 ሚሊዮን ዶላር ብድር የተገዙት 49 የወደብ ማሽኖች ኢትዮጵያ ገቡ

ADDIS ABABA, ETHIOPIA - APRIL 4 : Ethiopian Transport Minister Dagmawit Moges speaks during a press conference on "Boeing 737 Max 8" crash in Addis Ababa, Ethiopia on April 4, 2019. (Photo by Minasse Wondimu Hailu/Anadolu Agency/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የወደብ አገልግሎትን ያቀላጥፋሉ በሚል የተገዙ 49 የወደብ ማሽኖች ወደ ሀገር ቤት ገብተው ርክክክብ መካሄዱ ተሰማ።

የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን የሚመራው ሎጅስቲክስ ማዕከል የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ከሀምሌ 2009 ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር ላይ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ አካል የሆነው እና የሞጆ ደረቅ ወደብ አቅምን ለመገንባት፣ ብሎም ለማዘምን የሚያስችሉ 49 የወደብ ማሽኖች ግዢ ተፈፅሞ ዛሬ የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ተካሂዷል።
ማሽኖቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ 19 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ብድር ግዢው የተፈፀመ ሲሆን የፕሮጀክቱን 13 በመቶ እንደሚሸፍኑ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY