“አኖፌለስ ስቴፈንሳይ” የተሰኘች ወባ አስተላላፊ ትንኝ በኢትዮጵያ ከተሞች ተገኘች

“አኖፌለስ ስቴፈንሳይ” የተሰኘች ወባ አስተላላፊ ትንኝ በኢትዮጵያ ከተሞች ተገኘች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– አኖፌለስ ስቴፋንሰይ የተሰኘችው ወባ አስተላላፊ ትንኝ በኢትዮጵያ የተለያዮ ከተሞች ውስጥ መገኘቷ በጥናት ተረጋግጧል ተባለ።

በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የተለያዮ ከተሞች ውስጥ ትኖራለች የተባለችው “አኖፌለስ ስቴፈንሳይ” በእስያ በከተሞች አካባቢ ወባን በማስተላለፍ የምትታወቅ የትንኝ ዝርያ መሆኗም ተነግሯል።
የትንኝ ዝርያዋ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በምስራቅ የዓረብ ልሳነ-ምድር እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢዎች መገኘቷን የጠቆመው ጥናት፤ አሁን ደግም ይህች ትንኝ በጂቡቲ፣ በሱዳንና በሶማሊያ የተገኘች ከመሆኑ ባሻገር፤ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ2008 ዓ.ም በሶማሌ ክልል ቀብሪ ደሃር ከተማ እንደተገኘችም አስታውሷል።
የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አበበ ገነቱ የወባ ትንኟ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በምስራቅ ኦሮሚያና ምስራቅ አማራ በሚገኙ 10 ከተሞች መገኘቷን ገልጸው፤ ትንኟ ከዚህ ቀደም ባልተከሰተችባቸው የሰሜን ምስራቅ የአገሪቷ ከተሞች እየተስፋፋች ትገኛለች ብለዋል።

LEAVE A REPLY