ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (አዜማ) ቀጣይ ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚያስችለውን የምርጫ ማስፈፀሚያ የሚሆን 140 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው ገለጸ።
ለዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር እንዳዘጋጀ እና የካቲት 21 ቀን በግሎባል ሆቴል መርሀ ግብሩን ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን የኢዜማ የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዘላለምወርቅ አገኘሁ ተናግረዋል፡፡
በፕሮግራሙ የተዘጋጀውን ከ10 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ ትኬት በመግዛትም ደጋፊዎቹ ፓርቲውን እንዲያግዙ ከወዲሁ ጥሪ አቅርቧል።