ባለሀብቱ በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የዘይት ፋብሪካ በጠ/ሚ አብይ...

ባለሀብቱ በቀን 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የሚያመርት የዘይት ፋብሪካ በጠ/ሚ አብይ ተመረቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ በሁሉም ክልልች በስፋት የሚታየውን የዘይት አቅርቦት እጥረት ሊቀርፍ ይችላል የተባለ ግዙፍ ፋብሪካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ዛሬ በይፋ ተመረቀ።

በአማራ ክልል ቡሬ ከተማ የሚገኘው እና 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ይህ ፋብሪካ የጎጃም ተወላጅ በሆኑት ኢትዮጵያዊው ቢሊየነር በላይነህ ክንዴ ባለቤትነት የተገነባ ነው።
የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ አካል የሆነው ፌቤላ ኢንደስቱሪያል ኮምፕሌክስ  በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባ በቀን 1.5 ሚሊዮን ሊትር የዘይት ምርቶች ለኢትዮጵያ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዲይዝ ተደርጎ መገንባቱንም ሰምተናል።
በብዙኃኑ ሕዝብ ዘንድ የሚታየውን የዘይት ምርት ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት በውጪ ምንዛሬ፣ የዘይት ምርት ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ እያስገባ ባለበት በዚህ ወቅት የተገነባው ይህ ግዙፍ ፋብሪካ የሚያመርተው የዘይት መጠን 45 በመቶ የሀገሪቱን ፍላጎት እንደሚሸፍን
የኢንደስትሪያል ኮምፕሌክሱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዳምጤ ስማቸው ገልጸዋል።
ኮምፕሌክሱ ከቅባት እህሎች የሚመረቱ የዘይት ምርቶችን እና የፓልም ዘይትን ለገበያ የሚያቀርብ ሲሆን፤ ከቅባት እህሎች ለሚመረተው ዘይት ግብዓቱን ከሀገር ውስጥ ለመሰብሰብ እንደመታቀዱ ፋብሪካው ወደፊት ለቅባት እህል ዘይት ምርቱ የሚያስፈልገውን ግብዓት ለማግኘት የራሱን እርሻ እያዘጋጀ መሆኑም ታውቋል።

LEAVE A REPLY