ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የጀርመን መንግሥት ለምርጫ ሂደት ማስፈጸሚያ የ191 ነጥብ 58 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ።
ድጋፉ ለኢትዮጵያ መረጋጋት፣ ሰላም እና ብልጽግና አስተዋጽኦ የሚያደርግ እንደሆነም ከመግለጫው መረዳት ችለናል።
የጀርመን መንግሥት እ.ኤ.አ. ከ2020 እስከ 2025 ባለው የምርጫ ሂደት ፤ በአውሮፓ ኮሚሽን አማካኝነት በኢትዮጵያ ውጤታማ የምርጫ አስተዳደር እና አመራር እንዲኖር ድጋፍ አድርጓልም ተብሏል።