ከ20 ሺኅ የኤርትራ ስደተኞች ከትግራይ ጠፍተዋል መባሉን መንግሥት አስተባበለ

ከ20 ሺኅ የኤርትራ ስደተኞች ከትግራይ ጠፍተዋል መባሉን መንግሥት አስተባበለ

Oromo family hangs out their laundry at a camp for those displaced outside Adama, Ethiopia on Oct. 4, 2017. Fighting between Ethiopia's Oromo and Somali regional states has led to tens of thousands of people being internally displaced in camps around the country. (Photo by Paul Schemm for The Washington Post)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ቁጥራቸው ከሀያ ሺኅ የሚልቅ የኤርትራ ስደተኞች ከመጠለያቸው ጠፍተዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሳሳተ እና ከእውነት የራቀ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ።

ከአንድ ሳምንት በፊት በትግራይ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ 20 ሺኅ የኤርትራ ስደተኞች ከህጻጽ እና ሽመልባ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ጠፍተዋል የሚል ዜና ሰሞኑን በስፋት ሲናፈስ መሰንበቱ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል የሚገኙ ሁለት የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን በቅርቡ ልትዘጋ መሆኑን የስደት እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ አስታውቋል።
ሽመልባ መጠለያ የተመሰረተበት ቦታ ከኢትዮ-ኤርትራ ድንበር በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለመዘጋቱ በምክንያትነት ሲጠቀስ፣ በበረሃማ ቦታ የሚገኘው ህጻጽ፤ ለኑሮም ሆነ ለስደተኞች መጠለያነት አስቸጋሪ በመሆኑ አብሮ እንዲዘጋ መወሰኑ ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY