ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ የማኅበሩ ዋና ምሥሪያ ቤት ሆኖ የሚያገለግል ባለ 32 ወለል ህንፃ ሊገነባ መሆኑን ገለጸ።
የእድሜ ጠገቡ ማኅበር የዋና መሥሪያ ቤቱን ህንፃ የሚገነባው በአዲስ አበባ ከተማ ሲሆን ፤ ማኅበሩ እየተጠቀመበት የሚገኘውን አንድ ሺሕ 963 ካሬ ቦታ ዋና መስሪያ ቤት በሌላ ተለዋጭ ቦታ ለማስፋፋት ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም አስታውቋል።
የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት የሚገነባበትን የቦታ ማስፋፋፊያ ሥራ ማኅበሩ ከፌደራል ከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴር ጋር ውል ገብቶ እየሠራ እንደሚገኝ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ በንቲ ተናግረዋል።