ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ የሚገኙ 14 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጆች በመጪው እሁድ ከ6 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስመርቃሉ ተባለ።
የአስተዳደሩ የቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፤ በከተማዋ የሚገኙ ሥድሥት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆችና ስምንት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስመርቁ አረጋግጠዋል።
የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ በሚካሄደው የምረቃ ስነ-ስርዓት ኮሌጆቹ በ11 የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ከሁለት እስከ አራት ዓመት ያሰለጠኗቸውን 6 ሺህ 800 ተማሪዎች ነው ያስመረቁት።