ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ህንፃ የህወሓትን መደምሰስ ተከትሎ ወደ እናቶች እና ሕጻናት ሆስፒታልነት ተቀየረ።
በኢትዮጵያ ግዙፍ እና ትልቁ የሆነው የሕጻናት እና እናትች ሆስፒታል፤ በ20 ሺሕ ካሬ ላይ ያረፈ ሲሆን ከ400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች፣ 100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች፣በተመሳሳይ ሰዐት ለ7 እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ክፍሎችን ይዟል።
ዘመናዊና ወረቀት አልባ መስተንግዶ የሚሰጠው ይህ ሆስፒታል ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶች እንዲሟሉለት ተደርጓል። ግንባታው ቀድሞ ለመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ተብሎ የተጀመረ ቢሆንም፣ ትልቅ የአገልግሎት ችግር የእናቶች እና ሕጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት ሠባት መቶ ሚሊየን ብር በመመደብ ተጨማሪ ግንባታ በማድረግ እና ነባሩን ግንባታ በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር መደረጉም ታውቋል።