ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የአውሮፓ ሕብረት በትናንትናው መግለጫው የኤርትራ ጦር ከትግራይ እንዲወጣ ግልጽ ጥያቄ አቅርቧል።
የህወሓት የጥፋት እንቅስቃሴን ተከትሎ፣ በድንገተኛው ጥቃት ወደ ኤርትራ የሸሹ የሰሜን እዝ አባላት ጋር በመልሶ ማጥቃት የተወሰነ የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ መግባቱ አይዘነጋም።
ከቀናት በፊት የአሜሪካ ስቴትስ ዲፓርትመንት የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ ለቆ እንዲወጣ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።
የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በሰጠው መግለጫ ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለው ነገር ባይኖርም፤ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ባለስልጣናት የኤርትራ ጦር በትግራዩ ግጭት ተሳትፎ አላደረገም ማለቱ አይዘነጋም።