ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ጥቃት የደረሰባት ሉሲ ካሳ በኢትዮጵያ ውስጥ የመዘገብ ፈቃድ እንደሌላት መንግሥት አስታወቀ።
ከቀናት በፊት በመኖሪያዋ ጥቃት እንደደረሰባት የተናገረችው ጋዜጠኛ ሉሲ ካሳ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን የመዘገብ ፈቃድ እንዳልነበራት እና እንደሌላት የአስቸኳይ ጊዜ የመረጃ አጣሪው አካል አስታወቀ።
ለዓለም ዐቀፍ ሚዲያ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ፈቃድ ማግኘት እንደሚኖርባቸው የሚያስፈልግ ቢሆንም፤ ሉሲ ግን ይህ ፈቃድ ሳይኖራት ስትሠራ ቆይቷል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ መንግሥት ሁሉም ሰው ነፃ የመሆን መብት እንዳለው ጠቅሶ፤ ነገር ግን በድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በመንግሥት ላይ የተነሳውን ጣት ቅሰራ ቡድኑ እንዲያነሳ እና ማስተካከያ እንዲያደርግ መንግሥት ማሳሰቢያ ሰጥቷል።